፮. ገብር ሔር ፡- ገብር ሔር ማለት መልከም ባርያ ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው ፡፡ በዚህ ሳምንት የተጣለባቸውን አደራ ተቀብለው በታማኝነት ኃለፊነታቸውን የተወጡ መልካም አገልጋዮች በጌታቸው ፊት መወደሳቸውና መሸለማቸው ይወሳል ፡፡
በአንጻሩ ደግሞ የተሰጠውን አደራ ቸል ብሎ ኃላፊነቱን ያልተወጣ እኩይ ሎሌ በጌታው መወቀሱና መቀጣቱ የሚነገርበት የሚወሳበት ሳምንት ነው ፡፡
ይህ ታሪክ በማቴዎስ ወንጌል በሰፊው ተብራርቶ ተነግሯል ፡፡ አስመ ከመ ብእሲ ዘይነግድ ወጸውኣ አግብርቲሁ ወወሀቦሙ ንዋዮ ይትገብሩ ቦቱ … ፡፡ ማቴ.፳፭ ÷ ፲፬ - ፴ ፡፡
በዚህ ገጸ ንባብ ላይ እንደተብራራው ለረጅም ጊዜ ወደ ሌላ ሀገር የሚሄድ ሰው አገልጋዮቹን ጠርቶ ከሄደበት እስኪመለስ ድረስ በንዘቡ ነግደው ፣ አትርፈው ፣ ሀብቱን አበርክተረው እንዲቆዩት እንደየአቅማቸው ለአንዱ አንድ ፣ ለአንዱ ሁለት ፤ ለአንዱም አምስት መክሊት በአደራ ሰጣቸው ፡፡ ከብዙ ዘመናት በኋላ ከሄደበት ተለምሶ ገንዘቡን ከነትርፉ እንዲመልሱለት ሲቆጣጠራቸው ታማኝነት ከጎደለው ከአንዱ ሀኬተኛ ባርያ በስተቀር ፤ ሁለቱ አገልጋዮች በትጋት ፣ በታማኝነት ፣ ወጥተው ፣ ወርደው ፣ እጥፍ አትርፈው ለጌታቸው በማስረከብ ተሸልመዋል ፡፡
እኛም ዐረፍተ ዘመን እስከሚገታን ድረስ ነግደን ልናተርፍ ፣ መክሊት ልናበረክት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሠርቶ የማትረፍ ኃላፊነት የተቀበልን በለአደራዎች ነን ፡፡
ውድ ክርስቲያኖች ፡- ይህን የተጣለብን ታላቅ አምላካዊ አደራና ኃላፊነት በታማኝነትና በትጋት እየተወጣን ያለን ስንቶቻችን ነን ?
ሁላችንም ከሁሉ አሰቀድመን ለሕሊናችን በመታዘዝ ሙያዊ ሥነምግባራችንን በታማኝነት መወጣት ይጠበቅብናል ፡፡ አብረን ለምንኖረው ቤተሰባችን ፣ በመሥርያ ቤት በሙያ ወይም በጉልበት ለምናገለግለው ማሕበረሰብና መንግሥት (ለወገን ፤ ለሀገር) ፣ ለሃይማኖታችን ፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፣ ለፈጣሪያችን እውነተኛ ታማኝ አገልጋዮች መሆን ይጠበቅብናል ፡፡
ሳምንቱ የሽልማትና የቅጣት ሳምንት ስለሆነ ጌታችን ለፍርድ ሳይመጣ ለሽልማት እንትጋ የሳምንቱ የማኅቶት መልእክት ነው ፡፡
እለቱ መዝሙር ፡- መኑ ውእቱ ገብር ሔር
ምንባብ ፡-1ቆሮ. ð ፥ 1 - ፮ ፤ 2ጴጥ. í. ፥ í – ñ ፤ የሐዋ. ñ፥ í – %í
ምስባክ ፡- ይትሌቃህ ኃጥእ ወኢይፈዱ ወፃድቅሰ ይምሕር ወይሁብ እለ ይባርክዎ ይወርስዋ ለምድር ፡፡ መዝ. øò(øó) ፥ ÷í -÷2
ወንጌል ፡- ማቴ. ፳ñ ፥ %4 - '
ወስብሐት ለእግዚእብሔር
No comments:
Post a Comment