|
3.
ምኩራብ
፡- ሶስተኛው እሁድ ምኩራብ ነው ፡፡
በዚህ ሰንበት ጌታ ወደ ምሁራብ ገብቶ ማስተማሩ ነገራል ፤ ይወሳል ፡፡ ወደ ቅፍረናሆምም
ገቡ ፤ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማረ ፡፡ ማር .1 ፥ ÷1
፡፡ |
ምኩራብ የኤሁድ ቤተ ጸሎት ናት
፡፡ በአይሁድ ሕግ ከኢየሩሳሌም ውጭ ቤተ መቅደስ መሥራት አይፈቀድም ፡፡ ምክንያቱም ቤተ መቅደስ የታቦተ ጽዮን መኖሪያ ስለሆነች
፡፡ ታቦተ ጽዮን የነበረችው ደግሞ ኢየሩሳሌም ነበር ፡፡ ከኢየሩሳሌም ውጭ የነበሩ ቤተ አይሁድ በያሉበት ቦታ ምኩራብ ሠርተው ይጸልዩባት
፤ ትንቢተ ነቢያትን ፤ ሕግጋተ ሙሴን ይማሩባት ነበር ፡፡ በአንፊጶልና በአጶሎንም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ ፤ በዚያም የአይሁድ
ምኩራብ ነበረ ፡፡ የሐዋ. %ó ፥ 1
፡፡ እነዚህ
ከኢየሩሳሌም ውጭ የነበሩ ቤተ አይሁድ በዐመት አንድ ጊዜ ለክብረ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር ፡፡ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ
በሆነ ጊዜ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ ፡፡ ሉቃ. 2 ፥ (2
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በዚህ ሰንበት ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ሥጋዊ ንግድን በጅራፍ ገርፎ ከቤተ መቅደስ አስወግዷል ፡፡ ጅራፍ የመቅሰፍትና የቁጣ ምሳሌ ነው ፡፡ የአይሁድ
ፋሲካም ቀርቦ ነበር ፣ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ ፡፡ በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ፤ ርግቦችንም የሚሸጡትን ፣ ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ ፤ የገመድ ጅራፍም አበጅቶ
፤ ሁሉን በጎችንም ፣ በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው ፤ የለዋጮችንም
ገንዘብ አፈሰሰ ፣ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ ፣ ርግብ ሸጮችንም፡- ይህን ከዚህ ውሰዱ ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው
፡፡ ዮሐ. 2 ፥ %3 - %6
፡፡
ወገኖቼ ክርስቲያኖች ዛሬም ክርስቶስ
የቁጣ ጅራፍ ይዞ ሳይመጣ በቤተ ክርስቲያን የምናከሄደውን ሥጋዊ ንግድ ሁሉ በንሥሐ አስወግደን ክርስቲያናዊ ተግባራትን እንፈጽም
፡፡
የእለቱ መዝሙር ፡- ቦዐ ኢየሱስ
ምኩራበ አይሁድ
ምንባብ ፡- ቆላ. 2 ፥ %6-÷3 ፤ ያዕ. 2 ፥ %ô-÷í ፤ የሐዋ. Ñ öó-÷1
ምስባክ ፡- እስመ ቅንዓተ ቤትከ
በልዓኒ ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዓየሩከ ወድቀ ላእለየ ወቀጻዕክዋ በፆም ለነፍስየ ፡፡ መዝ. ፷ô(፷õ) ፥ õ -ö
wNg_L ፡- ዮሐ. 2 ፥ ö2 - ÷
No comments:
Post a Comment